የደቡብ ክልል ምክር ቤት ጉባኤውን ነገ ያካሂዳል


ሐምሌ 25/2013 (ዋልታ) –
የደቡብ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት 5ኛ ዙር 6ኛ አመት የስራ ዘመን 13ኛ መደበኛና ማጠቃለያ ጉባኤ ነገ ያካሂዳል፡፡
በጉባኤው የክልሉ መንግስት የ2014 በጀት ዓመት የስራ እቅድ ይቀርባል እንዲሁም የክልሉ መንግስት የ2014 በጀት በክልሉ ምክርቤት ይጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የክልሉ ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፤የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2013 አፈጻጸምና የ2014 በጀት አመት እቅድም የሚቀርብ ይሆናል ተብሏል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ልዩ ልዩ አዋጆች ይፀድቃሉ ለዳኞች ሹመት ይሰጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከክልሉ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡