የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

መስከረም 28/2014 (ዋልታ) የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡
ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የጥቅምት ወር የነዳጅ ምርቶች ችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንደሚቀጥል ሚኒስቴሩ ይፋ አድርጓል።
የአውሮፕላን ነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በመስከረም ወር አንድ ሊትር ሲሸጥበት ከነበረው 45 ብር ከ76 ሳንቲም ወደ 47 ብር ከ43 ሳንቲም ከፍ እንዲል የተወሰነ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በሌላ በኩል በዓለም ገበያ ላይ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደ አስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑም ተጠቁሟል፡፡