ጃፓን ለአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም የ820 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገች

ሰኔ 10/2013 (ዋልታ) – የጃፓን መንግስት ለአለም አቀፍ የሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ተቋም ለስልጠና የሚውል የ820 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገች።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) እና የጃፓን መንግስት በኢፌዴሪ ሰላም ማስከበር ማዕከል ከአለም አቀፍ ሰላም ማስከበር ማሰልጠኛ ማዕከል ጋር በጋራ ለመስራት የትብብር ሰነድ ተፈራርመዋል።

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ለማሰልጠኛ ተቋሙ ቴክኒካዊ ድጋፎችን ያደርጋል ተብሏል።

(በሱራፌል መንግስቴ)