ጠ/ሚ/ር ዐቢይ ከኖርዌይ አቻቸው ጋር ተወያዩ

ጥር 30/2014 (ዋልታ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኖርዌይ አቻቸው ጆናስ ጋህርስቶር ጋር ተወያዩ፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ጥልቅ ግንኙነት ጨምሮ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ውጤታማ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገፃቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ ኢትዮጵያ ከኖርዌይ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ አጋርነት ትገነዘባለች ብለዋል።