የአዲስ አበባ ስታዲየም የዕድሳት ስራ ተጀመረ

የአዲስ አበባ ስታዲየም ዕድሳት

ሰኔ 30/2013 (ዋልታ) –የአዲስ አበባ ብሄራዊ ስታዲየም የዕድሳት ስራ በዛሬው ዕለት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

የስታዲየሙን እድሳት ለማድረግ ከሁለት ሳምንት በፊት የውል ስምምነት የተደረገ ሲሆን፣ በውሉ መሠረት የእድሳት ስራው ዛሬ ተጀምሯል።

ዕድሳቱ በቅድሚያ ካፍ የሰጣቸውን አስተያየቶችን መሠረት አድርጎ እንደሚሰራና የመጫወቻ ሜዳው፣ የመልበሻና የመታጠቢያ ክፍሎች፣ የተመልካች መፀዳጃ እና የኤሌክትሪክ እና የሳኒታሪ ስራዎችን እንደሚያካትት ከስፖርት ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡