ብሩንዲ ኤርትራን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸነፈች


ሐምሌ 14/2013(ዋልታ) – ከ23 ዓመት በታች የሴካፋ የእግር ኳስ ውድድር ብሩንዲ ኤርትራን 3 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡
በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት አየተካሄደ ያለው ከ23 ዓመት በታች የሴካፋ የእግር ኳስ ውድድር በባህርዳር ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
ዛሬ ማለዳ ባህር ዳር የገባው የታንዛኒያ ብሔራዊ ቡድን ምድብ ሀ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ጋር 10 ሰዓት ላይ ጨዋታውን እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡