በቤልጂየምና ሉግዘምበርግ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ህብረት ፊት ለፊት ሰልፍ አደረጉ

ነሐሴ 07/2013 (ዋልታ) – በቤልጂየምና ሉግዘምበርግ እንዲሁም በአካባቢው በሚገኙ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵታውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በአውሮፓ ህብርት ፊት ለፊት ሰልፍ አደረጉ፡፡

ሰልፉን በቤልጂየም የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበራት ያስተባበሩት ሲሆን፣ ሰልፈኞቹ ‘ከኢትዮጵያ ላይ እጃችሁን አንሱ፣ ‘የሃሰት ፕሮፓጋንዳን አቁሙ’፣ ‘የአውሮፓ ህብረት ከኢትዮጵያ ህዝብ ጎን መቆም አለበት’፣ ‘ህጻናትን ለውትድርና መመልመልን እንቃወማለን’፣ ‘በአፋር ህዝብ ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ እንቃወማለን’ እንዲሁም ‘ህወሃት የተኩስ አቁሙን ባለመቀበል በህዝቦች ላይ የጦር ወንጀል ፈጽሟል’ የሚሉ መልዕክቶችን አስተጋብተዋል።

ከዚህም በተጨማሪ ሰልፈኞቹ ህወሃት በማይካድራና በአፋር የፈጸመውን ጭፍጨፋ የሚያሳዩ ፖስተሮች ይዘው በመውጣት አሸባሪው ህወሃት የሚፈጽማቸውን ድርጊቶች ማሳየታቸውን ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ አመልክቷል።