በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር የብር ሜዳሊያ ተገኘ

ነሃሴ 13/2013 (ዋልታ) – በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ ባለው 18ኛው ከ20 ዓመት በታች የዓለም የአትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያ በ5 ሺህ ሜትር የወንዶች ውድድር  የብር ሜዳሊያ አግኝታለች።

ለኢትዮጵያ የብር ሜዳሊያውን   በአትሌት ታደሰ ወርቁ አማካኝነት ያገኘች ሲሆን በሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት አዲሱ ይሁኔ 4ተኛ ደረጃ ማግኘቷን ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።