አምባሳደር ጀማል በከር ከዓለም አቃፍ የስደተኞች ድርጅት ኃላፊ ጋር ተወያዩ

ነሀሴ 21/2013 (ዋልታ) – በባህሬን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስል ጄነራል አምባሳደር ጀማል በከር በባህሬን የተባበሩት መንግስታት ድርጅቶች ተወካይና የዓለምአቀፍ የስደተኞች ድርጅት ኃላፊ መሀመድ አልዛርካኒ ጋር በትብብርና በቅንጅት አብሮ ለመስራት በሚያስችል ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡
አምባሳደር ጀማል በከር በኢትዮጵያ ወቅትታዊ ሁኔታ ዙሪያ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በመካከለኛ ምስራቅ አገራት ውስጥ ለተለያዩ ችግር የተጋለጡ ኢትዮጵያዊያን ዜጎችን ለማገዝ እያደረጉ ላሉት እንቅስቃሴ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የሰው ሃይል የውጭ አገር የስራ ስምሪት ከመነሻ እስከ መዳረሻ ያለውን ሰንሰለት የዜጎችን መብትና ጥቅም ሊያረጋግጥ በሚያስችል መልኩ እየተደረገ ያለውን ጅማሮ አድንቀዋል፡፡
በተያያዘም አምባሳደር ጀማል በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ባህሬን የሚመጡትንና በአገሪቷ ውስጥ አልፎ አልፎ የሚደርሱ ችግሮችን እንዲፈቱ ከድርጅቱ ጋር በቅርበትና በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡
የአለም አቃፍ ድርጅቶች ኃላፊ መሀመድ አልዛርካኒ የተገደረገላቸውን ገለጻና አድንቀዋል፡፡
በተለያዩ ድርጅተቸው የመካከለኛ ምስረቅ አገራት ውስጥ በኢትዮጵያ ዜጎች ላይ የሚደርሰውን የደህንነትና የመብት ጥሰቶችን ለመፍታት በቀጣይ የበለጠ ጥረት እንደሚያደርጉ ገልጸዋል፡፡
በተለያዩ ምክንያቶች በባህሬን ለችግር የሚጋለጡትን ኢትዮጵያን ዜጎች ለመርዳት ዝግጁ መሆናቸውን እንዳረጋገጡ ከውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል፡፡