ፊፋ የኡጋንዳ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትን ለሁለት ወራት አገደ

የኡጋንዳ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት የሆኑት ሞሰስ ማጎጎ ከማንኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ለሁለት ወራት መታገዳቸውን ፊፋ አስታውቋል።

ፕሬዝዳንቱ ለሁለት ወራት ከማንኛውም የእግር ኳስ እንቅስቃሴ ከመታገዳቸው በተጨማሪ የ10 ሺህ ዶላር መቀጮ ይከፍላሉ ተብሏል።

ፕሬዝዳንቱ ቅጣቱ የተጣለባቸው በኡጋንዳ የ2014 የዓለም ዋንጫ ትኬት መልሶ በመሸጡ ነው ተብሏል። (ምንጭ፡- ቢቢሲ)