የሩዋንዳ ሴቶች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ባህርዳር ገባ

መሰከረም 23/2014 (ዋልታ) የሩዋንዳ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን ባህርዳር ገባ።
ቡድኑ 23 ተጫዋቾችን ጨምሮ 36 አባላትን የያዘ ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በመጪው ረቡዕ ለሚያደርገው ጨዋታ ባህርዳር መግባቱን የኢትዮጰያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን መረጃ አመላክቷል።
የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ወደ ሩዋንዳ አቅንቶ 4 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፎ መመለሱ ይታወሳል።