ቃልኪዳን ገዛኸኝ የ10 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች

መስከረም 23/2014 (ዋልታ) ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቃልኪዳን ገዛኸኝ የ10 ሺህ ሜትር የዓለም ክብረ ወሰን ሰበረች።

ለባህሬን የምትሮጠው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ቃልኪዳን ገዛኸኝ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ በተካሄደ ውድድር ነው ክብረ ወሰን የሰበረችው።

አትሌቷ 29:38 በሆነ ሰዓት በመግባት ክብረ ወሰን መስበሯን ከወርልድ አትሌቲክስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።