ለ17ኛ ጊዜ በኳታር ዶሃ በተካሄደው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የተሳተፈው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ቡድን አዲስ አበባ ገብቷል፡፡
ዛሬ ከማለዳው 1፡30 ላይ አዲስ አበባ ቦሌ ኤርፖርት ሲደርስ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚነኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ሚነኒስትር ዴኤታ አቶ ሀብታሙ ሲሳይ፣ የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ስፖርት ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ ጌታቸው ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክሰ ፌዴሬሽን ም/ፕሬዝዳንት አትሌት ገ/እግዚአብሄር ገ/ማርያም እንዲሁም የአትሌቲክስ የሙያ ማህበራትና ክለብ አመራሮችን ጨምሮ የስፖርት ቤተሰቡ በተገኘበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎለታል፡፡
ቡድኑ በቆይታው ሁለት ወርቅ ፣ አምስት ብር እና 1 ነሃስ በድምሩ 8 ሜዳሊያዎችን በማግኘት ከዓለም 5ኛ ከአፍሪ 2ኛ በመሆን ውድድሩን ማጠናቀቁ ይታወሳል፡፡