39ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች ውድድር ነገ ይጀምራል

የካቲት 14/2014 (ዋልታ) 39ኛው የፔፕሲ አዲስ አበባ የክለቦች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር ነገ በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ይጀመራል።

20 ክለቦች የሚሳተፉበት የአዲስ አበባ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከየካቲት 15 እስከ 20 ድረስ ለስድስት ቀናት እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው።

ከ1 ሺሕ 200 በላይ አትሌቶች በሚሳተፉበት ሻምፒዮና ጥሩ ፉክክር ይኖራል ተብሎ ይጠበቃል።

የአዲስ አበባ ክለቦች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ውድድር በ1975 ዓ.ም ጀምሮ ነው መካሄድ የጀመረው፡፡

በሚኪያስ ምትኩ