ሚያዝያ 12/2014 (ዋልታ) በአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታ የኢትዮጵያ ተጋጣሚዎች ተለይተው ታወቁ።
በ2023 የኮትዲቧር የአፍሪካ ዋንጫ ለመሳተፍ ለማጣሪያ ጨዋታ ምድብ ድልድል ከደቂቃዎች በፊት ይፋ ሆኗል።
በዚህም መሰረት ዋልያዎቹ በምድብ 4 ከማላዊ፣ ጊኒ እና ግብፅ ጋር ተደላድላለች።
42 ሀገራት በ12 ምድቦች ተከፍለው በሚጫወቱበት የማጣሪያ መርኃ ግብር ከየምድባቸው አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃን ይዘው የሚያጠናቅቁ ብሔራዊ ቡድኖች የአፍሪካ ዋንጫን የሚቀላቀሉ ሲሆን የማጣሪያ መርኃ ግብሩ የፊታችን ሰኔ ወር ላይ ይጀምራል።
በመሠረት ተሰፋዬ
ለፈጣን መረጃዎች፦
ቴሌግራም https://t.me/WALTATVEth
ዩቲዩብ https://www.youtube.com/c/WaltaTV/featured
ቲዊተር https://twitter.com/walta_info
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!