ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ድሉ በሐምሌ ጨለማ የፈነጠቀ የተስፋ ብርሃን ነው አሉ

ሐምሌ 21/2014 (ዋልታ) የአትሌቶች ታላቅ ድል በሐምሌ ጨለማ የፈነጠቀ የተስፋ ብርሃን ነው ሲሉ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ገለጹ፡፡

በኦሪገን የዓለም አትሌትክስ ሻምፒዮና ውድድር ላይ ለተሳተፉ የአትሌትክስ ቡድን አባላት በብሔራዊ ቤተ መንግሥት በተደረገው የሽልማት መርኃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት ፕሬዝዳንቷ ውጤቱ ተስፋ ለቆረጡ፣ ለተጨነቁ፣ ኑሮ ለከበዳቸውና በተለያዩ ውጣ ውረድ ውስጥ ላሉ ዜጎች ደስታ የፈጠረና እፎይታ የሰጠ ነው ብለዋል።

የኢፌዴሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስትር ቀጄላ መርዳሳ በበኩላቸው የተገኘው ውጤት የአትሌቶች የአላማ ጽናት ማሳያ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በውድድሩ ወቅት አትሌቶች ያሳዩት የትብብርና የመደጋገፍ መንፈስ የሚደነቅ መሆኑንም አንስተዋል።