ፍቅረማርያም ያደሳ ለ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበለት

ሐምሌ 14/2016 (አዲስ ዋልታ) ኢትዮጵያዊው ቡጢኛ ፍቅረማርያም ያደሳ ባገኘው የብር ሜዳሊያ ለ2024 ፓሪስ ኦሎምፒክ እንዲሳተፍ ጥሪ ቀረበለት።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድንን በመወከል በ57 ኪሎ ግራም የቡጢ ተወዳዳሪው ፍቅርማርያም ያደሳ በሴኔጋል ዳካር ተካሂዶ በነበረው የ2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ የማጣሪያ ውድድር ላይ ለፍፃሜ በመድረስ የብር ሜዳሊያ ማስመዝገቡ ይታወሳል፡፡

ሆኖም የወርቅ ሜዳሊያ በማግኘት ለፓሪስ ኦሎምፒክ ውድድር ያለፈው ናይጄሪያዊው ኦሞሎ ዶላፓ ባጋጠመው የጉልበት ጉዳት የተነሳ መሳተፍ ባለመቻሉ ፍቅረማርያም ያደሳ ባገኘው የብር ሜዳሊያ  በፓሪስ ኦሊምፒክ እንዲሳተፍ ጥሪ መቅረቡን የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል።