ቴክኖ ቅምሻ – ዲፕ ፌክ ቴክኖሎጂ

ሀሰተኛ መረጃዎች በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወሩ ማየት የተለመደ እየሆነ መጥቷል፡፡ እነዚህ ሀሰተኛ መረጃዎች ዲፕ ፌክን በመጠቀም ተዘጋጅተው ይሰራጫሉ፡፡

ዲፕ ፌክ የሰው ሰራሽ የነርቭ አውታረ መረቦችን (Artificial Neural Network) በመጠቀም ፊትና ድምጽ መቀየር የሚያስችል የሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ ውጤት ነው፡፡

ብዙውን ጊዜ ቴክኖሎጂው ግለሰብ ነባር አሊያም ተመሳሳይ ፎቶ፣ ቪዲዮ ወይም ድምጽን በግብዓትነት በመጠቀም ሰውየው ያላደረገውን ወይም ያልተናገረውን ሲሰራ ወይም ሲናገር አዲስ ይዘት ለመፍጠር ይውላል፡፡

ዲፕ ፌክ የሚያደርሰው ትልቁ አደጋ ከታመኑ ምንጮች የመጡ የሚመስሉትን ሐሰተኛ መረጃዎችን የማሰራጨት ችሎታቸው ነው።

እንደ ቴክታርጌት ዘገባ ይህ ቴክኖሎጂ በምርጫ ቅስቀሳ ላይ ጥቅም ላይ ሊውልና የምርጫ ውጤት እስከማዛባት የሚደርስ ስጋትም አስነስቷል።

ዲብ ፌኮች ከባድ ወንጀሎችን ለመፈጸም ስጋት ቢሆኑም የቪዲዮ ጌም ድምጽና መዝናኛ፣ የደንበኛ ድጋፍ እና የደዋይ ምላሽ መተግበሪያዎች እንደ የጥሪ ማስተላለፍ እና መቀበያ አገልግሎቶች ያሉ ጥቅሞች አሏቸው።