ነሐሴ 27/2016 (አዲስ ዋልታ) በ17ኛው የፓራሊምፒክ ጨዋታዎች አትሌት ያየሽ ጌቴ በ1500 ሜትር ሴቶች የአይነ ስውር (T-11) ፍጻሜ በማሸነፍ ለኢትዮጵያ በውድድሩ ሁለተኛውን የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።
አትሌት ያየሽ 4 ደቂቃ ከ27 ሴኮንድ ከ68 ማይክሮ ሴኮንድ በራሷ ተይዞ የነበረውን የዓለም ክብረ ወሰን በአራት ሴኮንድ በማሻሻል ነው ውድድሩን ያጠናቀቀችው።
ያየሽ ከዚህ ቀደም በጃፓን ኮቤ በተካሄደው 11ኛው የዓለም የፓራአትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ 4 ደቂቃ ከ31 ሴኮንድ ከ77 ማይክሮ ሴኮንድ በማስመዝገብ የዓለም ክብረ ወሰንን ይዛ እንደነበር ይታወሳል።
አትሌት ትዕግስት ገዛኸኝ በ1500 ሜትር ሴቶች የጭላንጭል (T-13) ፍጻሜ ለኢትዮጵያ በውድድሩ የመጀመሪያውን የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቷ ይታወቃል።