ሚኒስቴሩ ዴንማርክ ለታዳሽ ኃይል ልማት 4ሚሊዮን ዶላር መስጠቷን አስታወቀ

ዴንማርክ ለኢትዮጵያ ታዳሽ ኃይል ልማት ማበልፀጊያ 4 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ  ማድረጓን ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስቴር  አስታወቀ ።

ሁለቱ ሀገራት በዘርፉ ተባብረው ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ትናንት በአዲስ አበባ  ማድረጋቸውን ነው የገለጸው ።

ስምምነቱ የኢትዮጵያን ታዳሽ ኃይል በተለይም በንፋስ ኃይል ልማትና የአገሪቱን የኃይል ስርጭት አገልግሎት ጥራት እንዲኖረው የሚያግዝ መሆኑን አመልክቷል ።

ስምምነቱን በኢትዮጵያ በኩል የፈረሙት  የፋይናንስና ኢኮኖሚ  ትብብር ሚንስትር ድኤታ አቶ አድማሱ ነበበ ስምምነቱ የታዳሽ ኃይሉ  ልማት  ለማሳደግ የተሰጠውን ትኩረት የሚደግፍ መሆኑን ገልጸዋል ። 

በዴንማርክ በኩል የዴንማር አምባሳደር በኢትዮጵያ የትብብር ስምምነቱ  መፈረማቸውን ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ትብብር ሚንስቴር  የተገኘውን መረጃ   የጠቀሰው  የኢብኮ ዘገባ  አመልክቷል