በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ወይይት እየተካሄደ ነው

በኢትዮጵያ ንግድ ህግ ማሻሻያ ረቂቅ ዙርያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግብዓት ማሰባሰቢያ ጥናትና ውይይት  እየተከናወነ መሆኑን የፌደራል አቃቢ ህግ አስታወቀ ፡፡

በአገሪቱ በ1952 ዓ.ም የወጣው የንግድ ህግ ባለፉት 58 ዓመታት ያህል በስራ ላይ የዋለ ሲሆን ከ1983 አንስቶ በመተግበር ላይ ያለው ገበያ መር የኢኮኖሚ ሥርዓት የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ከመደገፍና ከማሳደግ አኳያ የሚነሱ ተያያዠ እጥረቶችን ለመቅረፍ አሁን በመሻሻል ላይ ያለው ህግ ትልቅ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ከ2006 ዓ.ም አንስቶ በመሻሻል ላይ ያለውን የንግድ ህግ ከባለድርሻ አካላት የሚነሱ የግብዓት ሓሳቦችን አካቶ ለሚመለከተው የመንግስት አካል እንደሚያቀርብ ታውቋል፡፡ 

 የፌዴራል አቃቤ ህግ የህግ ጥናት ማርቀቅና ማስረፅ ዳይሬክተር አቶ በላይሁን ይርጋ ህጉ ከአንድ ሺ በላይ አንቀፆችን ያቀፈ መሆኑን ገልፀው  አምስት የንደፈ ሀሳብ መፃህፍት መዘጋጀታቸውንና  የይይዘት ማጣጣም ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

የማሻሻያ ህጉ ኢትዮጵያን ወደ አለም አቀፍ የንግድ አባልነት አንድትቀላቀል ዘመናዊ አሰራር እንዲኖራት ያስችላል ተብሏል፡፡