የባንኮች አጠቃላይ ተቀማጭ ሂሳብ ከ 688 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱ ተገለጸ

በኢትዮጵያ የባንኮች አጠቃለይ ተቀማጭ ሂሳብ ከ688 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገለጸ።

በባንኩ የገንዘብና ፋይናንስ ትንተና ዳሬክተር አቶ ሙሉነህ አያሌው እንዳሉት፥ የባንኮችን ተቀማጭ ሒሳብ ለማሳደግ የተለያዩ እርምጃዎች ተወስደዋል።

ከእነዚህም መካከል የባንኮችን አገልግሎት ተደራሽነት የማስፋት እርምጃ አንዱ ነው፡፡

ቆጣቢዎች የሚያገኙትን የወለድ ጥቅም ለመጨመር የወለድ መጠን ከ5 በመቶ ወደ 7 በመቶ ከፍ ማድረጉ ሌላኛው ምክንያት መሆኑን ነው ያነሱት።

በዚህም እስከ መጋቢት 2010 ዓ.ም ድረስ በአገሪቱ የባንኮች አጠቃላይ ተቀማጭ ሒሳብ ከ688 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱንና ይህም ባለፈው ተመሳሳይ ወቅት ከነበረው 529 ቢሊየን ብር ፤ በዚህ ዓመት የ30 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ተናግረዋል፡፡ (ኢዜአ)