ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት አዲስ መለያ ይፋ አደረገ

ዋልታ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬት አዲስ ያሰራዉን የተቋሙን መለያ አስተዋውቋል፡፡

ተቋሙ በኩሽቲክ ስቱዲዮ የተሰራወን አዲሱን መለያ በትላንትናው እለት ተረክቧል።

የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ተተካ በቀለ አዲሱ የመለያ ምልክት ማሻሻያ ያስፈለገዉ ተመልካቾች በተደጋጋሚ ባቀረቡት ጥያቄና ተቋሙ ከጊዜዉ ጋር እንዲራመድ ለማስቻል መሆኑን ገልፀዋል።