አሜሪካ 6ሺ የሚደርሱ የቻይና ምርቶች ላይ የ200 ቢሊዮን ቀረጥ መጣሏን አስታወቀች

አሜሪካን 6ሺ  በሚደርሱ የቻይና ምርቶች ላይ የ200 ቢልዮን ዶላር ቅረጥ ጥላለች ተመጣጣኝ ምላሽ ሰጥታለች።

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶላንድ ትራምፕ ቻይና በሀገሬ ላይ ያላት የንግድ የበላይነት በጣም በዝቷል ገደብ ሊኖረው ይገባል በሚለው አቋማቸው ምክንያት በቻይና ሸቀጦች ላይ የ25በመቶ ቀረጥ ጥላለች ።

የሁለቱ ሀያላን ሀገራት የንግድ ውዝግብ አንዳቸው ለአንዳቸው ምላሽ እየሠጡ አሁን ላይ ወደለየለት የንግድ ጦርነት ገብተዋል ። የሁለቱ ሀገራት ውዝግብ የአለምን ኢኮኖሚ እያቃወሰው እንደሚገኝም ኢኮኖሚ ተንታኖች ያናገራሉ።

ባሳለፍነው ነሐሴ ወር ሁለቱ ሀገራት በንግድ እንቅስቃሴያቸው ዙሪያ ለመነጋገር ቀጠሮ ቢይዙም እግሮቻቸውን ይፈታል የተባለው ድርድር ሳይሳካ  ቀርቶ አሜሪካን በቻይና ላይ 34 ቢሊዮን  ዶላር ከ300 የተለያዩ ምርቶች ላይ ለመሰብሰብ ስትወስን ቻይናም 16 ቢሊዮን ዶላር ከ270 የተለያዩ ምርቶች ላይ ለመሰብሰብ በማቀድ ምላሽ  መስጠቷ አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ አሜሪካን  ስማርት ሰአቶች፤ የልጆች መጫወቻዎች፤ሳይክሎችን ጨምሮ በ6ሺህ  የቻይን ምርቶች ላይ 200 ቢሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ማቀዷን ተከትሎ ቻይና ከአሜሪካን በምታስገባቸው እንደ ስጋ፤የአልኮል መጠጦች፤ማሽነሪዎች ልብሶችን ጨምሮ 5ሺህ በሚደርሱ የተለያዩ ምርቶች ላይ 60 ቢሊዮን ዶላር እንደምትሰበስብ አስጠንቅቃለች ።

አሁን ላይ አሜሪካን  ከቻይና፤ከአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት፤ከካናዳ፤ከሜክሲኮና ከቱርክ ጋር ከገባችበት የንግድ ቅራን በተጨማሪ ከአለም የንግድ ድርጅት እራሷን  ማግለል እንደምትፈልግ ተናግራለች።

በተቃራኒው ቻይና የንግድ ግንኙነቷን ከተለያዩ ሀገራት ጋር በፍጥነት እያጠናከረች ትገኛለች።አሁን ላይ አሜሪካን በንግድ እንቅስቃሴዋ ከአለም ሀገራት በሚያስችል ደረጃ እየተገለለች መምጣቷ ይህ ደግሞ በቻይና ላይ ያላትን አቋምና ከአለም የንግድ ድርጅት እራሳን ማግለል የማታነሳ ከሆነ ይበልጥ ዋጋ ያስከፍላታል ተብሎ ተፈርቷል።

ይህ የዋሽንግተንና የቤልጂንግ የንግድ ጦርነት  በሀገራቸው ግዙፍ ካንፓኒዎች ላይ እያደረሱት ካለው ተፅእኖ በተጨማሪ የአለም ኢኮኖሚ እድገት ቀርፋፋ እንዲሆን አድርጎታል።

በዚህ የንግድ ውዝግብ ምክንያት ሁለቱ ሀገራት በቢሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር ለታክስ ወጭ ማድረጋቸው ታውቋል። በተለይ ደግሞ አሜሪካን በኤሌክትሮንክስ ምርቶች በጣለችው ቀረጥ ምክንያት የፊልም ካምፓኒዎቿ ጫና ውስጥ መግባታቸው ይነገራል።

የአለምን ኢኮኖሚ በበላይነት የሚመሩት እነዚህ ሁለቱ ሀገራት አሁን ላይ የገቡበት ውጥረት የአለምን የንግድ እንቅስቃሴ ከማዳከም ባለፈ የበላይነቱን ማን ይይዛል ማን አሸንፎ አዛዥነቱን ይቆናጠጣል የሚለው ይበልጥ አጓጊ አድርጎታል።( ምንጭ: ከሲኤን ኤን)