የኢትዮጵያን ባለልዩ ጣዕም ቡና ምርቶችን በንግድ ምልክትነት የማስመዝገብ ሥራ ተሠርቷል

የኢትዮጵያን ባለልዩ ጣዕም ቡና  ምርቶች  በዓለም አቀፍ ደረጃ  በንግድ ምልክትነት የማስመዝገብ  ሥራ  መሠራቱን  የአዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት አስታወቀ ።                             

የኢትዮጵያን ባለ ልዩ ጣዕም የቡና ምርቶች ከ2004ዓም ጀምሮ በንግድ ምልክትነት ከማስመዝገብ ባሻገር ወጥ አሰራር ተክተሎ ጥቅም ላይ ከማዋል ጋር ተያይዞ ችግሮች እያገጠሙ መሆኑም ተገልጿል ።

የጽህፈት ቤቱ የአዕምሯዊ ንብረት እሴት ልማታዊ ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ወርቁ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ከ2004 ዓም አንስቶ የኢትዮጵያን ባለ ልዩ ጣዕም ቡና ማለትም የሲዳማ፤ ይርጋ ጨፌና የሀርር ቡናዎችን በተለያዩ የኢትዮጵያ ቡና ገዢዎችና ተጠቃሚ ሀገራት ዘንድ በንግድ ምልክትነት የማስመዘገብ ሥራ ተሠርቷል፡፡

በተለይም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተመዘገቡት የቡና ምርቶች ሂደታቸውን ጠብቀው አርሶ አደሩና ሀገር ተጠቃሚ እንዳይሆኑ አስቀድሞ በተቀረፀው ፕሮጀክት ዙሪያ የሚሰሩ ባለድርሻ አካላት በርካታ መሆናቸው ጉዳዩ ትኩረት እንዳያገኝ ካደረጉ ምክንያቶች መካከል አንደሚጠቀስ ዳይሬክተሩ አያይዘው ገልፀዋል፡፡

የኢትዮጵያ አዕምራዊ ንብረት ፅህፈት ቤት አእምራዊ ንብረት በቂ የህግ ጥበቃ እንዲያገኝ፤ ሀገር በቀል የፈጠራ ስራዎች እንዲበራከቱ፤ የቴክኖሎጂ ሽግግር እንዲፈጠር፣ ባህል እንዲከበር እንዲሁም ፍታሃዊ የንግድ ውድድር እንዲሰፍን የተለያዩ ሥራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡