በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ

በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ማድረጉን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ለዋልታ በላከው መግለጫ በአለም ላይ ያለውን የነዳጅ ምርቶች ዋጋ ጭማሪን ግምት ውስጥ በማስገባት በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ መጠነኛ ጭማሪ ማድረጉን ነው የገለጸው።

በዚህ መሰረት ቤንዚን በሊትር 19 ብር ከ 69 ሳንቲም፣ ነጭ ናፍጣ በሊትር 17 ብር ከ78 ሳንቲም፣ ነጭ ጋዝ በሊትር 17 ብር 78 ሳንቲም፣ ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 15 ብር ከ41 ሳንቲም፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 14 ብር ከ90 ሳንቲም ሆኗል፡፡

የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በሊትር 27 ብር ከ08 ሳንቲም ሲሆን÷ የነዳጅ ችርቻሮ መሸጫ ዋጋው ከህዳር 4 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሃገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ማደያዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስቴሩ ጨምሮ ገልጿል።