አየር መንገዱ ለ7ኛ ጊዜ የአፍሪካ የምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለ7ኛ ተከታታይ ጊዜ የአፍሪካ የምርጥ አየር መንገድ ሽልማትን አሸነፈ።

አየር መንገዱ ሞሮኮ ራባት ላይ በመካሄድ ላይ ባለው 50ኛው የአፍሪካ ታላላቅ አየር መንገዶች ማህበር አመታዊ ጉባኤ ላይ አሸናፊ መሆኑ ተገልጿል ።

የእውቅናው ሽልማቱ ለአየር መንገዱ  በፋይናንስና ትርፋማነት አፈጻጸም  ላይ ባሳየው የላቀ ደረጃ ምክንያት እንደተበረከተለት ተነግሯል።

የኢትዮዽያ አየር መንገድ  ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ከሽልማቱን በኋላ በማስመልከት ባደረጉት ንግግር፥ ድርጅቱ የእውቅና የሽልማቱ አሸናፊ በመሆኑ በጣም ደስተኛ  መሆናቸውና፥ ሽልማቱን ላበረከተው ለአፍሪካ የአየር መንገዶች ማህበርና እህት አየር መንገዶች ምስጋና አቅርበዋል።

ሽልማቱ የአየር መንገዱ ሠራተኞች ያልተቋረጠ ከፍተኛ ጥረት፣ ትጋትና ርብርብ ውጤት መሆኑን አንስተዋል።

በተጨማሪ የእውቅና ሽልማቱ የተቋሙን ፈጣን፣አትራፊና ዘላቂነት ያለው የእድገት እቅድ፣ የራእይ 2025 እንዲሁም ተያያዥ የሆነው የቢዝነስ ሞዴሎችን  ውጤታማነት የሚያሳይ ነው ብለዋል።