2ኛው የኢትዮ-ግሪክ ቢዝነስ ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል

ሁለተኛው የኢትዮ-ግሪክ ቢዝነስ ፎረም  በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል።
በቢዝስ ፎረሙም 14 የሚደርሱ ቀዳሚ የግሪክ ኩባንያዎች መሳተፋቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ኩባንያዎቹ በቱሪዝም፣ በኢንዱስትሪ ፣ በኢነርጂና በመሰረተ ልማት ግንባታ ዘርፎች ለመሰማራት ፍላጎት ያላቸው መሆኑ ነው የተገለፀው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር አክሊሉ ሐይለሚካኤል ሁለቱ ሀገራት ላለፉት ዓመታት ያዳበሩት ጠንካራ ወዳጅነት በንግድና ኢንቨስትመንትም መደገም አለበት ብለዋል።

የግሪክ ባለሃብቶች በግብርና፣በኢነርጂ፣ በቱሪዝም እና ምግብ ማቀነባበር ዘርፎች ቢሰማሩ ውጤታማ እንደሚሆኑና መንግስትም አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው ገልጸዋል።

የግሪክ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኒኮላስ ኩይክ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ፖሊሲና ለኢንቨስትመንት ያላትን ምቹ ሁኔታ  አድንቀዋል።

በመካሄድ ላይ ያለው ቢዝነስ ፎረም ግሪክ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማሳደግ ላላት ቁርጠኝነት አይነተኛ ማሳያ ነው ብለዋል።

በፎረሙ ላይ የኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማህበራት ከግሪክ ኢንተርፕራይዞች ፌደሬሽን ጋር ተቀራርቦ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት