የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ቱርክ ኢስታንቡል የቀጥታ በረራ አገልግሎት ሊጀምር መሆኑን አስታውቋል፡፡
አየር መንገዱ ከሰኞ መጋቢት 23 ቀን 2011 ዓ.ም. ጀምሮ ወደ ቱርክ ኢስታንቡል በሳምንት 3 ቀናት ይበራል ነው የተባለው፡፡
ኢስታንቡል የቱርክ ታሪካዊ፣ የኢንዱስትሪ እና የፋይናንስ ከተማ እንደሆነች ይነገርላታል፡፡
የኢስታንቡሉ ቀጥታ በረራ የአውሮፓ 19ኛው መዳረሻው ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአጠቃላይ በአምስቱም አህጉራት 119 መዳረሻዎች አሉት፡፡