የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ” ሽልማትን አሸነፈ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሩዋንዳ ኪጋሊ በተደረገ የአፍሪካ አየር መንገዶች ስራ አስፈፃሚዎች ፎረም ላይ “የአመቱ የአፍሪካ ምርጥ አየር መንገድ” ሽልማትን አሸንፏል፡፡

የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ተወልደ ገብረማሪያም ሽልማቱን ተቀብለዋል፡፡

ሽልማቱ የአየር መንገዱን አለምአቀፋዊና አህጉራዊ ተወዳጅነት ያስጠበቀ ሲሆን በቅርቡ የተከሰከሰውና ለ157 ሰዎች ህይወት ማለፍ መንስዔ ከሆነው ክስተት ማግስት የተገኘ ነው፡፡

(ምንጭ፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ)