ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ264 ሚሊየን ዶላር የቀላል ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ264 ሚሊየን ዶላር ቀላል ብድር ማቅረብ የሚያስችል የማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከናወኑ የልማት ፕሮክቶች የሚውል ሲሆን፥ የደቡብ ኮሪያ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ተፈራርመውታል።

የመጀመሪያው የ170 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት በደቡብ ኢትዮጵያ ለሚገኘው የብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍሰትና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት የሚውል መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

በዚህም በኢትዮጵያ በሰሜን ምዕራብ ለሚገኙ የሀገሪቱ ክፍሎችና እና ለኦሞ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ፣ ለአርባምንጭ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታም እና የመስኖ ልማትና የገጠር ልማት ፕሮጀክቶች እንደሚውል ተጠቅሷል፡፡

በዚህም አርሶ አደሩ የግብርና ምርቱን እንዲያሳድግና ገቢው እንዲጨምር ያደርጋል ተብሏል፡፡

(ምንጭ ፡- የገንዘብ ሚኒስቴር)