የግንቦት ወር የነዳጅ ምርቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ተደረገ

የንግድ ሚኒስቴር የግንቦት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ ከሚያዚያ 30 ቀን እስከ ግንቦት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆነውን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ አድርጓል።

በተደረገው የዋጋ ክለሳ መሰረትም በአዲስ አበባ ከተማ

ቤንዚን …………………………………………..21 ብር ከ53 ሳንቲም በሊትር

ኢታኖል ድብልቅ ቤንዚል……………………….21 ብር ከ19 ሳንቲም በሊትር
ነጭ ናፍጣ ……………………………………18 ብር ከ75 ሳንቲም በሊትር
ኬሮሲን……………..…………………………18 ብር ከ75 ሳንቲም በሊትር
ቀላል ጥቁር ናፍጣ……………………………….16 ብር ከ67 ሳንቲም በሊትር
ከባድ ጥቁር ናፍጣ……………………………….16 ብር ከ24 ሳንቲም በሊትር
የአውሮፕላን ነዳጅ ……………………………….25 ብር ከ90 ሳንቲም በሊትር እንዲሆን ተወስኗል።

የተደረገውን የዋጋ ማስተካከያ በሚመለከት ሚኒስቴሩ የህዝብ ማስታወቂያ ያዘጋጀና በዚሁ የህዝብ ማስታወቂያ የተካተቱ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ዝርዝር በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚታተም መሆኑንም አስታውቋል።

አዲሱ የዋጋ ማስተካከያ ከሚያዚያ 30 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎች በሚገኙ ነዳጅ ማደያዎች ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑ በመግለጫው ተገልጿል፡፡