ኬንያ በተያዘው ፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ነዳጅ ወደ ውጪ ገበያ ልታቀርብ ነው፡፡

ቱሎው ኦይል ቱሎው በተባለችው የአየርላንድ ከተማ የተመሰረተ ሲሆን ዋና መቀመጫውን እንግሊዝ ለንደን ያደረገ በነዳጅ ፍለጋ ላይ የተሰማራ ኩባንያ ነው፡፡

ኬንያ፣ ኡጋንዳ፣ ጋና እና ፈረንሳይን ጨምሮ በ25 ሃገራት ውስጥ 67 የምርት መስኮች ያሉት ኩባንያም ነው፡፡

ኩባንያው በፈረንጆቹ 2012 በኬንያ ባደረገው ፍለጋ ሃገሪቷ የተከማቸ የነዳጅ ሃብት እንዳላት ይፋ አድርጓል፡፡

ኩባንያው ባደረገው ፍለጋ በምሥራቅ አፍሪካ አገራት ውስጥ በአሁኑ ጊዜ ለሽያጭ ሊቀርብ የሚችል 750 ሚሊዮን በርሜል የሚገመት ነዳጅ እንዳለ አረግግጫለው ብሏል፡፡

እንደ ሲጂቲኤን ዘገባ ኩባንያው ከሆነ ኬንያ በ2019 ሶስተኛ ሩብ ዓመት ነዳጅ ወደ ውጪ መላክ ትጀምራለች፡፡

መግለጫውን የሰጡት በምስራቅ አፍሪካ የቱሎው ዘይት ምክትል ፕሬዚዳንት ማርክ ማክፋርላን እንደገለጹት÷ በግንቦት ወር በተደረገው ቅድመ ሙከራ የዘይት ምርቱ በቀን ከነበረበት 600 በርሜል ወደ 2 ሺህ በርሜል አድጓል፡፡

ምክትል ፕሬዚዳንቱ አክለውም ወደ ውጪ ገበያ የሚቀርበው የነዳጅ ዘይት  ኬንያ በነዳጅ ምርት የምታገኘው የውጭ ምንዛሬ ገቢ እንዲያድግ ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል፡፡

በዓመቱ መጀመሪያ አጋማሽ ላይ  የላይኛው እና የመካከለኛው የማምረቻ ክፍል የምህንድስና ዲዛይን ጥናቶች መጠናቀቃቸውን ማክፋርሌን ገልፀዋል፡፡ ፡፡