ለሁለት ቀናት የሚቆይ የኢ-ኮሜርስ ኤግዝቪሽን ተከፈተ

ለሁለት ቀናት የሚቆይ የኢ-ኮሜርስ ኤግዝቪሽን በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን አዳራሽ በዛሬው ዕለት ተከፈተ፡፡

ዝግጅቱን ያስተባበረው ፓልኮን ኢንዱስትሪያል ማርኬቲንግ በኢትዮጵያ ያለውን የፋይናንስ ሴክተር በዲጅታል ቴክኖሎጂ ለማስተሳሰር የበኩሉን እየተወጣ መሆኑን ገልጿል፡፡

በኢግዝቪሽኑ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የዲጅታል ፋይናንስ ተቋማት መንግስት ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ እየወሰደ ያለው የህግ ማሻሻያ ዘርፉን እያሳደገና ህብረተሰቡንም የኢ-ኮመርስ አገልግሎት ተጠቃሚ እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለሁለት ቀናት በሚቆየው በዚሁ ኤግዝቪሽን የንግድ ማህበረሰብ፣ አስመጪና ላኪዎች፣ ኢንቨስተሮች እና የማይክሮፋይናንስ ተቋማት ይሳተፉበታል ተብሏል፡፡

ኢ ኮሜርስ ግብይትን በኢንተርኔት አማካኝነት ማካሄድ የሚያስችል አገልግሎት ሲሆን፤ በንግድ ልውውጡ ክፍያዎችንና ዳታዎችን በኢንተርኔት አማካኝነት መለዋወጥ ያስችላል።