የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በበጀት አመቱ ከዕቅድ በላይ ማትረፉን ገለፀ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት በተሰማራባቸው ዘርፎች ስኬታማ በመሆንና በሚሰጣቸው የጠቅላላ የመድን ሽፋን አገልግሎት በ2011 በጀት አመት ከእቅድ 27 ነጥብ 4 በመቶ ብልጫ በማስመዝገብ ፤ ከታክስ  በፊት 854  ነጥብ 7 ሚሊየን ብር ትርፍ ማስመዝገቡን አስታውቋል ።

ድርጅቱ የ2011 በጀት አመት  እቅድ አፈፃፀም በገመገመበት ወቅት  9 ነጥብ 1 ቢሊየን የአርቦን መጠን ወይንም ከመደን ሽፋን የተገኘ ሲሆን ፤ ይህም ከኢንዲስትሪ መድን ሽፋን ከህይወት መድን እንዲሁም ከጠቅላላ መድን  ሽፋን መሆኑን ነው የተነገረው ።

የድርጅቱ  ደንበኞች ለደረሰባቸው  የህይወት እና ንብረት አደጋ  የከፈለው የካሳ ክፍያ  1 ቢሊየን ሲሆን ፤ ይህም ካለፈው አመት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ ካሳ የተከፈለበት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የሀገሪቱ ፓለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ አለመረጋጋት ፣ የትራፊክ አደጋ መጨመር እና የውጭ ምንዛሬ ተመን ክለሳ ጋር ተያይይዞ የመለዋወጫ እቃ መጨመርን የመሳሰሉ ችግሮች ቢኖሩም በመስሪያ ቤቱ ማኔጅመንትና ሰራተኞች ጥንካሬ ተቋሙ ለስኬት እንደበቃ  ተገልጿል፡፡

የሳተላይት ቢሮዎችን ጨምሮ እስካሁን የአጠቃላይ ቅርንጫፍ ቢሮዎች ቁጥር  102 መድረሱ የተገለፀ ሲሆን፤  በቀጣይም አዲስ የመድን ሽፋን ለመክፈትና ተደራሽነትንም ለማስፋት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ተቋሙ አስታውቋል፡፡