የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ልዩ ቅርንጫፍ ከፈተ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውንና የሸሪዓ ህግን ተከትሎ ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የሚሰጥ ልዩ ቅርንጫፍ ከፈተ።

ቅርንጫፉ ቢላል ቅርንጫፍ በሚል ስያሜ በዛሬው ዕለት ቦሌ ሚካኤል አካባቢ በይፋ መከፈቱን ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ቅርንጫፉ በተመረቀበት ወቅት የባንኩ ፕሬዚዳንትና ሥራ አስፈፃሚ አቶ ባጫ ጊና፣ የባንኩ የሸሪዓ አማካሪ ኮሚቴ አባላትና ደንበኞች ተገኝተዋል።