ኢትዮጵያ እና ቻይና በትምህርት ዘርፍ ያላቸውን ትብብር አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተገለፀ

31 የቻይና ዩኒቨርሲቲዎች የተሳተፉበት ኤግዚቢሽን በአዲስ አበባ ተከፍቷል።

በስካይ ላይት ሆቴል በተከፈተውና ለአንድ ቀን በሚቆየው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ የተገኙት የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሂሩት ወ/ማርያም፤ ሁለቱ ሀገራት የጀመሩትን ሁለንተናዊ ትስስር በትምህርት ዘርፉ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጁዋን በበኩላቸው፤ ቻይና በኢትዮጵያ የትምህርት ዘርፍ የምታደርገውን ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ኤግዚቢሽኑ በኢትዮጵያ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎች ከቻይና ዩኒቨርስቲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር የትምህርት ዕድል እንዲያመቻቹ መልካም ዕድል ይፈጥራል ተብሏል፡፡