100 ተጨማሪ አዳዲስ አውቶቢሶች ወደ ስራ ሊገቡ ነው

በአዲስ አበባ 100 ተጨማሪ አዳዲስ አውቶቢሶች ወደ ስራ ሊገቡ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አውቶቢሶቹ በአሁን ወቅት በአዲስ አበባ ያለውን የትራንስፖርት እጥረት ለማቃለል አስተዋፆኦ እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡

አውቶቢሶቹ ከነገ ማለትም መስከረም 14፣2012 ዓ.ም ጀምሮ መግባት እንደሚጀምሩም ነው የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅ/ቤት መረጃ የሚያመለክተው፡፡

በከተማዋ ያለውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍ የብዙሃን ትራንስፖርት አንበሳ እና ሸገር ባስ አገልግሎትን ለማሻሻል በጥናት ላይ የተመሠረተ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው፡፡

ከዚህ ተጨማሪ የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊ አውቶቢሶች ከውጪ ለማስገባት እና የትራንስፖርት ስምሪቱን ዘመናዊ የሚያደርግ አሰራር ለመዘርጋት እየሰራ ነው፡፡