አልዛይመር በሽታን ከአሥር ዓመት ባነስ ጊዜ ውስጥ መቆጣጣር እንደሚቻል ተጠቆመ

የአልዛይመር በሽታን ልክ እንደኤች አይቪ ኤድስ በሽታ ሁሉ በአጭር ጊዜ ውስጥ መቆጣጣር እንደሚቻል በበሽታው ላይ ምርምር ያደረጉት ፕሮፌሰር ባርት ዲ ስትሮፐር ተናገሩ ።

 በእንግሊዝ የለንደን ዩኒቨርስቲ ኮሌጅ  እውቅ ተመራማሪ የሆኑት ቤልጄማዊ ፕሮፈሰር ባርት ዲስትሮፐር  በትናንትናው ዕለት እንደተነበዩት  የአልዛይመር ወይም የመርሳት በሽታን   በአሥር ዓመት ውስጥ  በቁጥጥር ሥር መዋልና የሚያስከትለውን ጉዳት  መቀልበስ እንደሚቻል ገልጸዋል ።

ፕሮፌሰሩ እንደሚገልጹት ምንም እንኳን የአልዛይመር በሽታን ማዳን እንደማይቻል የተረጋጋጠ ቢሆንም እ.ኤ.አ በ2025 የአልዛይመር በሽታን  ልክ እንደኤች አይቪ ኤድስ በሽታ በተለያዩ ህክምና ዘዴዎች የሚያስከትለውን ጉዳት መቀነስ ወደ ሚቻልበት ደረጃ እንደሚደረስ አስረድተዋል ።     

ዓለም አቀፍ ከእርጃና ጋር በተያያዘ ጥናትና ምርምር የሚያደርገው ዳመንሺያ ወርልድ ባለፈው ወር  የመጀመሪያ የሆነውን የአልዛይመር በሽታ ላይ ውጤታማ ህክምና ለመሥጠትና  መድሃኒቱን ለማግኘት  የሚያስችለው ምርምር ሙከራ ውጤት አልባ መሆኑ  ከታየ በኋላ ነው ይህ አስተያያት የተሠጠው  ።

እንደ  ፕሮፌሰር ዲ ስትሩፐር ገለጻ  ለአልዛይመር በሽታ የሚሆን  ሌላ መድሓኒት  ጊዜውን ጠብቆ እኤአ በ2025 አካባቢ ሊመጣ እንደሚችል የተለያዩ ቀደም ሲል የተከናወኑ  ምርምሮች ያመለክታሉ ብሏል ።      

እ.ኤ.አ  በ2013  የቀድሞ  የእንግሊዝ  ጠቅላይ ሚኒስትር  ዴቪድ ካሜሮን በአልዛይመር  በሽታ  ላይ ለሚካሄደውን ምርምር   የሚመደበው በጀት እንዲጨምር  ቃል መግባታቸውና   ፍቱን  መድሃኒትም እንዲገኝለት ያለሰለስ ጥረት እንደሚያደርጉ መቀለጹ ትልቅ ተስፋን የሰነቀ  እንደነበር ፕሮፌሰሩ አስታውሰዋል ።

(ምንጭ: www. dailymail.com )