አዲሱ የፕሮስቴት ካንሰር የሌዘር ህክምና ተስፋ ሠጪ እንደሆነ ተገለጸ

የፕሮስቴት ካንሰር የቀዶ ጥገና ባለሙያዎች በሌዘር ቴክኖሎጂ  የሚካሄደው አዲሱ የፕሮስቴት ካንሰር  ህክምና ተስፋ ሰጪ መሆኑን  ገልጸዋል ።

ህክምናው በመላው አውሮፓ የተሞከረና ዘመናዊ የሌዘር ቴክኖሎጂንና ከጥልቅ ባህር በተገኘ ባክቴሪያ  የቀመረ  መድሓኒትን በመጠቀም  ካንሰሩ የሚፈጥውን እብጠት ምንም ጉዳት ሳያስከትል መከላከል የሚያስችል  ነው ።    

በ413 ሰዎች ላይ የተደረገው ሙከራ እንደሚያሳየው ከግማሽ በላይ በጥናቱ የተካተቱት የአዲሱ ህክምና ተካሚዎች ከካንሰር በሽታው ነጻ ሆነው ተገኝተዋል ። እስካሁን ድረስ  የፕሮስቴት ካንሰርን በቀዶ ጥገናና በራዲዮ ቴራፒ የህክምና ዘዴ ለሚሠጠው ህክምና  ወንዶችን  የማህንነት  ሲዳርግ መቆየቱ ተገልጿል ።               

በአዲሱ የህክምና ዘዴ የተሻለ ውጤት  ለማግኘት በፕሮስቴት ካንሰር  የተጠቁ ወንዶች የካንሰቱ እብጠት  ከፍ ከማለቱ በፊት ወደ ህክምናው  መምጣት እንዳላባቸው  የህክምናው ዘዴው  ላይ  ሙከራ  እያደረጉ ያሉት ፕሮፈሰር  ማርክ  ኢምበርተን ይናገራሉ ።     

አዲሱ የፕሮስቴት ካንሰር ህክምናው ከሚዋጥ መድሓኒት በተጨማሪ  አሥር የሚሆኑ ኦፕቲክ ሌዘሮችን በመጠቀም የፕቶስቴር ግላንድን  በደንብ  ከስር መሠረቱ ለመፈተሽ የሚያስችል የህክምና ዘዴ ነው ።

በተለያዩ የአውሮፓ ሆስፒታሎች  የህክምናው ሙከራ  ከተካሄደባቸው  47 ሰዎች መካከል 49 በመቶ የሚሆኑት  ሙሉ ለሙሉ ካንሰሩ የፈጠረው እብጠት የቀነሰላቸው ሲሆን  6 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ የካንሰሩ እብጠት የማስወገድ ሥራ የሚያስፈልጋቸው ሆነዋል ።

በተነጻጻሪነት  ቀደም ሲል  ሌላ አይነት የፕሮስቴት ካንሰር ህክምና ከሚከታተሉት ውስጥ   30  በመቶ የሚሆኑት እብጠቱን የማስወገድ ህክምና የሚያስፈልጋቸው  በመሆኑ  አዲሱ  ህክምናን የተሻለ ያደርገዋል ተብሏል ።    

የ 68 ዓመት የዕድሜ ባለፀጋ የሆነው ጄራርድ ካፖን ለቢቢሲ እንደተናገረው በአዲሱ ህክምና ዘዴ   ሙሉ ለሙሉ መዳኑንና ከካንሰሩ ነጻ እንደሆነ ገልጿል ።

በተጨማሪም ለህክምናው ለሙከራ የቀረብኩ ቢሆንም  እድለኛ በመሆኔ  ድኛለሁ  ከህክምናውም በኋላ ከሆስፒታል  መውጣቱን ተናግሯል ።

እንደ ፕሮፌሰር ኤምበርቶን ገለጻ  አዲሲ በቴክኖሎጂ የታገዘው ህክምና ጥቅሞችንና ጉዳቶችን  በማመዛዘን የሚካሄድ መሆኑንና ከህክምናው በኋላ  በወንዶች ላይ ከሚያስከትላቸው  አሉታዊ ጉዳቶች ነጻ ስለሚያደርጋቸው  ህክምናው ወደ አንድ እርምጃ ያሸጋጋረ ነው ብለውታል ። 

(ምንጭ : ቢቢሲ)