በማህፀን ጫፍ ካንሰር ክትባት ዕጦት ሩብ ሚሊዮን ሴቶች ለሞት እንደሚዳረጉ አለምአቀፉ የካንሰር ምርምር ድርጅት አስታወቀ።
የአለም ጤና ድርጅት አካል የሆነው አለም አቀፉ የካንሰር ምርምር ድርጅት እንዳለው እንደ ድርጅቱ ሪፖርት ከሆነ በማህፀን ጫፍ ካንሰር ምክንያት በየአመቱ ሩብ ሚሊዮን ሴቶች ለሞት ይዳረጋሉ።ከዚህ ውስጥ ደግሞ 85 በመቶ የሚሆኑት ሞት የክትባቱን መድሃኒት መግዛት በማይችሉ በአነስተኛና መካከለኛ ገቢ ባላቸው አገራት የሚኖሩት እንደሆነ ድርጅቱ ገልጿል።
በመሆኑም እንደድርጅቱ ገልፃ የተጠቃሚዎችን አቅም ያገናዘበ የካንሰር ክትባት ማቅረብ በማህፀን ጫፍ ካንሰር በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠርን የእናቶችን ሞት ለማሰቀረት ያስችላል።
በተለይም አገራት እንደ ማህፀን ጫፍ ካንሰር ላሉ በሽታዎች ለሚቀርቡ ክትባቶች ትኩረት ሰጥተው የዜጎቻቸውን ህይወት መታደግ እንዳለባቸው የአለም አቀፉ የካንሰር ምርምር ድርጅት አስገንዝቧል።