ወንዶች ልጅ እንዳያስወልዱ የሚያደርገው የህክምና ዘዴ በዝንጀሮዎች ላይ ተሞክሮ ውጤት ማምጣቱ ተገለጸ
አዲሱ የቫሳል ጅል ቴክኖሎጂ የወንዶች የዘር ህዋስ በወንዶች የዘር ፍሬ ማስተላለፊያ ትቦ እንዳይፈስ በመከላከል ከግንኙነት በኋላ እርግዝና እንዳይኖር የሚያደርግ ነው ተብሏል ።
ሙከራውን የሚያደርገው ኩባንያ እንደገለጸው በሁለት ዓመታት የሙከራ ጊዜ ውስጥ አዲሱ የቫሳል ጅል ቴክኖሎጂ በዝንጀሮዎች በተከታታይ ተሞክሮ ውጤት አምጥቷል ።
በቀጣይ ዓመታትም ሙከራውን ከዝንጀሮ ወደ ሰው የማሻገር ሥራ እንደሚከናወን ተጠቅሷል ።
እንደ ኩባንያው ገለጻም ወንዶች እንዳያስወልዱ የሚያደርገው ቴክኖሎጂ በሰዎች ላይ ውጤት ካመጣ በሚቀጥሉት አሥርት ዓመታት የዓለም ገበያውን የሚቆጣጠር የወንዶች እርግዝና መከላከል ዘዴ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል ።
በአሁኑ ወቅት በግንኙነት ወቅት እርግዝና እንዳይፈጠር ለማድረግ በወንዶች በኩል በስፋት ኮንዶምን የመጠቀም ሁኔታ ያለ ሲሆን የወንዶችን የዘር ቧንቧን በመቁረጥ ወይም በመቋጠር እንደ እርግዝና መከላከያነት ጥቅም ላይ ውለዋል ።
አዲሱ የወንዶች ወሊድ መከላከያ ካስኮቶሚ ወይም የዘር ቱቦን በመቁረጥ ከሚደረግ የህክምና ዘዴ የሚለየው የህክምና ተጠቃሚው ልጅ ማስወለድ በሚፈልግበት ጊዜ የወንዱን የዘር ፍሬ ወደነበረበት ለመመለስ ያስችላል ። ( ምንጭ: ቢቢሲ)