ከዚህ ቀደም እርጎን መውሰድ ምግብን በፍጥነት እንዲፈጭ እንደሚያደርግ ፣ ፊትን የሚያጸዳና ፀጉራችን እንዳይበጣጣስ የሚያደርግ መሆኑን የተለያዩ ተመራማሪዎች የገለጹ ሲሆን አዲስ የተደረጉ ጥናቶች እርጎ ድብርትን ለመከላከል ፍቱን መድሓኒት መሆኑን ጠቁመዋል ።
በእርጎ ክሬም ውስጥ ባክቴሪያን መሥራት የሚያስችሉ ንጥረ ነገሮች በብዛት የሚገኙ በመሆኑ አንድ ሰው እርጎን በሚወስድበት ጊዜ ሰውነቱ ውስጥ የደም ግፊትን በመቀነስ ፣ ጭንቀትና ውጥረትን እንዲቃለል ይረዳል ተብሏል ።
ተመራማሪዎች እንደሚገልጹት በእርጎ ውስጥ የሚገኘው ባክቴሪያ አመንጪ ንጥረ ነገር የሰው ልጅን ለድብርት የሚዳርገውን በደም ውስጥ ሜታቦሊት የተባለ ቅመም መጠንን የሚቀንስ ነው ተብሏል ።
በቨርጂኒያ ዩኒቨርስቲ የሜዲሲን ትምህርት ቤት ተመራማሪዎች እንደሚናገሩት የተለያዩ መርዛማ መድሓኒቶችን በመጠቀም ድብርትን ለመከላከል ሙከራ ከማድረገ ይልቅ እርጎን በመጠቀም ተፈጥሯዊ በሆነ ሁኔታ ድብርት ለመከላከል ጥረት ማድረግ የተሻለ እንደሆነ ይመክራሉ ።
የምርምሩ አስተበባሪ ዶክተር አለባን ጉትለር እንደሚገልጹት የሰው ልጅን ድብርት ላይ ጥናት በማድረግ ማንኛውም ሰው መልካም ስሜት ኖሮት ሥራውን እንዲያከናውን ለማስቻል እርጎን የመሳሰሉት የምግብ አይነቶችን በመጠቀም በደም ውስጥ የሚገኘውን ባክቴሪያ በማሳደግ ድብርትን መቆጠጣር ይቻላል ።
በአሜሪካ በዜጎች ላይ ከሚያጋጥሙ የአዕምሮ ጤና መታወክ ስክተቶች መካከል ድብርት ዋነኛውን ሥፍራ የሚይዝ መሆኑን ያመለከቱት ዶክተር ጉልቲየር ለድብርት ተብለው የሚሠጡ የህክምና አይነቶች ከባድ የጎንዮሽ ጉዳት ያሚያስከትሉና የህክምና አይነቶቹም ችግር ያለባቸው ናቸው ብለዋል ።
በተጨማሪም በቨርጂኒያ ዩኒቨርስቲ የኒሮ ሳይንስና የአዕምሮ ህክም ትምህርት ክፍል ባለድረባ የሆኑት ዶክተር ጉልቲየር እንደሚገልጹት እስካሁን ድረስ በድብርትና የሆድ እቃ ጤና ያላቸውን ግንኙነት በተጨባጭ ለማወቅ ጥናቶች እየተካሄዱ ነው ብለዋል ።
በግኝቱ መሠረት የሰው ልጅ በድብርት በሚያዝበት ወቅት በደም ውስጥ የሚገኘው ላክቶ ባሲለስ የተባለው ቅመም እንደሚጨምር በጥናት የተረጋገጠ ሲሆን በድብርት የተጋለጡ ሰዎች ከህክምናቸውንና መድሓኒታቸው ጎንለጎን እየተከታተሉ እርጉን በመውሰድ የተሻለ ጤናን ማግኘት ይችላሉ ።
(ምንጭ: ዴይሊ ሜል )