የቤት ውስጥ መገልገያዎች አካባቢና ጤና ላይ ይበልጥ ችግር የሚፈጥሩ መሆናቸውን ጥናቶች አመለከቱ

አብዛኛዎቹ የእጅ ሳሙናዎችና  ሌሎች  የቤት  መገልገያዎች በውስጣቸው ብዙዎች የጤና ጠንቅ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን  የያዙ መሆናቸው የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ  ፡፡

እነዚህን ኬሚካል ያላቸዉን የእጅና የገላ ሳሙናዎችን ደጋግመን ስንጠቀም ለጤና ችግር የሚያጋልጡና በሂደት ደግሞ ለካንሰር በሽታ የሚዳርጉ መሆኑን የተለያዩ ጥናቶች ያወጡት መረጃዎች ይጠቁማሉ  ፡፡

ከመጠን በላይ የሆኑ  ፀረ ባክቴሪያ ንጥረ ነገሮችን የያዙ  የእጅና የገላ ሳሙናዎችን  የጥናቶቹ ውጤቶች ይፋ ከተደረጉ በኋላ  የአሜሪካ   ምግብና  መድሓኒት  አስተዳደር  የተባለው ተቋም ወደ ገበያ እንዳይቀርቡ የሚያግድ ህግ አርቅቋል፡፡

የጥርስ ማፅጃ ቡርሾች ሙሉ በሙሉ ከፕላስቲክ የተሰሩ ሲሆን በአጠቃላይ በየዓመቱ 8 ሚሊዮን ቶን  የሚሆኑ የመገልገያ ፕላስቲኮች አካባቢዎችን እንዳይበክሉ በቀዳሚነት ወደ ውቅያኖሶች እና ባህሮች  የሚጣሉ  መሆኑን ይጠቀሳሉ፡፡

የኤስያ ሀገራት ከእንጨት የሚሰራውን ሹካ ለመመገቢያነት በመጠቀም ይታወቃሉ፡፡  በየአመቱ 57 ቢሊየን ሹካ ለማምረት  የኤሲያ አገራት 4 ሚሊየን ዛፎች  ይወድማሉ፡፡

እንደ ግሪን ፒስ የተባለዉ መንግስታዊ ያልሆነ የአካባቢ ጥበቃ ተቋም ሪፖርት ከሆነ ደግሞ  ሹካዎቹ የሚታጠቡት በኬሚካል በመሆኑ የአመጋገብ ስርዓት ላይ ችግር እንደሚፈጥሩ  የጥናቶቹ ውጤት  ያመለክታሉ ፡፡

በኬሚካል የረጠበ  ሶፍት ከቅርብ ግዜ ወዲህ እጅን ወይም ቆዳን ለማፅዳት በብዛት መጠቀም እየተለመደ  መጥቷል፡፡

በቀላሉ የማይቀደዱ የወረቀት ሶፍቶች  ተጠቅመን በምንጥላቸዉ ሰአት የዉሃ መተላለፊያዎችን እና ቱቦችን በመዝጋት እና በወንዞች  አካባቢ ግዙፍ ክምችት በመስራት የአካባቢ  ብክለትን  እንደሚፈጥሩ ይገለጻል ፡፡

በየቀኑ ለምንገበያያቸው እቃዎች መያዣነት የምንጠቀምባቸዉ ፌስታሎች አካባቢን በመበከል ቀዳሚዉን ድርሻ ይይዛሉ፡፡አንድ ትሪሊዮን የሚጠጉ ፌስታሎችበመላው ዓለም  በየአመቱ ይወገዳሉ፡፡

በተጨማሪም  ለተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች የምንጠቀማቸው  ባትሪዎችም  በውስጣቸው  የሚፈነዳና እንደ ሜሪኩሪ ሊድ እና ካዲየም የተባሉ ለሰው ልጅ  ጤና አደገኛ የሆኑ  ንጥረ ነገሮችን  በውስጣቸው  የያዙ ናቸው ፡፡  ባትሪዎቹ ጥቅም ከሠጡ  በኋላ  ወደ አፈር እና ዉሃ ውስጥ ተቀላቅለዉ ከፍተኛ የጤና ስጋት  የመሆን እድላቸው  ከፍተኛ  መሆኑን  ጥናቶቹ ያመላክታሉ ፡፡

ይህንን ስጋት ለመቀነስ  ባትሪዎችን ከመጠቀም ይልቅ ግን በኤሌክትሪክ ጃርጅ የሚደረጉ አማራጮችን መጠቀም የተሻለ ነዉ ተብሏል፡፡ (  ምንጭ : ሲኤንኤን )