በልብ ድካም የሚሰቃዩ ሰዎች ህክምናቸውን እንዲከታተሉ የሚያስችል አዲስ መተግበሪያ ይፋ ሆነ

በልብ ድካም የሚሰቃዩ ሰዎች ህክምናቸውን በአግባቡ እንዲከታተሉ የሚያስችል በዘመናዊ ስልኮች አማካኝነት የሚሰራ አዲስ መተግበሪያ ይፋ ማድረጉን የሲድኒ ዩኒቨርሲቲ አስታወቀ፡፡

በልብ ድካም የሚያሰቃዩ ሰዎች መድሃኒታቸውን በትክክል እንዲወስዱ፣ ከሃኪማቸው ጋር ለሚኖራቸው የህክምና ክትትል፣ ቀን እና ሰአታቸውን ለማስታወስ የሚረዳ መተግበሪያ ነው ይፋ የሆነው፡፡

ይህ የመጀመሪያው እና አዲስ መድሃኒት አስታዋሽ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች ለረዥም ጊዜ እንዲወስዷቸው ከሃኪም የታዘዘላቸውን መድሃኒቶችን በአግባቡ እንዲወስዷቸው የሚያግዝ እንደሆነ ነው ተገለፀው፡፡

አዲሱ ቴክኖሎጂ ከማንኛውም ከተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ በሰዓት ከሚሞሉ ‘‘የአሳውቀኝ’’ ወይም  ሪማይንደር እና ከቤተሰብ ወይም ከጓደኞች መድሃኒቱን መውሰጃ ሰኣታቸውን አልያም ቀነ ቀጠሮአቸውን እንዲያሳውቋቸው የሚገደዱበት ሁኔታን ሙሉ በሙሉ የሚቀርፍ ነውም ብለዋል፡፡

ወደፊትም እንደ  ደምግፊት እና ስትሮክ የመሳሰሉ ረዥም ዓመታት በሚቆዩ ሕመሞች ላይ ትኩረት ሰጥተው ምርምር እንደሚያደርጉም ተገልጸዋል፡፡ (ሲጂቲኤን)