የጤና ተቋማትን አገልግሎት ለማሻሻል ልዩ ልዩ ሪፎርሞች እየተሰሩ ናቸው

የጤና ተቋማትን አገልግሎት ለማሻሻል ልዩ ልዩ ሪፎርሞች እየተሰሩ እንደሆነ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአንስቲዢያ ህክምና ማህበር 14ኛውን አመታዊ ጉባኤን በንግግር የከፈቱት የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታዋ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የአንስቲዢያ ህክምና ተደራሽነትን በመላው አገሪቱ ለማዳረስ ከፍተኛ ጥረትና ርብርብ በመደረግ ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በአንስቴዢያ ዙሪያ የሚታዩ የግብዓት እጥረቶችን ለማቃለል እና ለህሙማን የጤና አገልግሎት ጥራት ተደራሽነት ልዩ ልዩ አዳዲስ አሠራሮችን ለመተግበር ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል፡፡

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴርም ከኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር ጋር በመቀራረብ ወደፊት ሊተገበሩ በተዘጋጁት የጤና ዘርፍ መርሆዎች ዙሪ አብሮ ይሰራል ብለዋል፡፡

14ኛው የኢትዮጵያ አንስቴቲስቶች ማህበር የአንስቴዢያ ባለሙያዎችን የእርስ በርስ ግንኙነት በማጠናከርና የልምድ ልውውጥ በማድረግ በዘርፉ የሚስተዋሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት የተዘጋጀ መሆኑን የማህበሩ ፕሬዘዳንት ረዳት ፕሮፌሰር ልዑልአየሁ አካሉ ገልፀዋል፡፡

በጉባኤው ላይ የተለያዩ ጥናታዊ ፅሁፎች የሚቀርቡ ሲሆን ከ400መቶ በላይ የአንስቲዢያ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል፡፡(ምንጭ: ጤና ጥበቃ ሚኒስትር)