የወባ ትንኝን የመራባት ኡደት የሚቆጣጠር መድኃኒት ማግኘታቸውን ተመራማሪዎች ይፋ አደረጉ

የአሜሪካ ሳይንትስቶች የወባ ትንኝን የመራባት ኡደት የሚቆጣጠር መድኃኒት ተግባራዊ ለማድረግ የመጨረሻው ደረጃ ላይ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።

የአሪዞና ዩንቨርስቲ አጥኚዎች እንደገለጹት ሴቷ የወባ ትንኝ ለመፈልፈል የሚያስፈልጋትን ፕሮቲን የተባለ ንጥረ ነገር ማስቆም ከተቻለ የምትጥላቸው እንቁላሎች መፈልፈል አይችሉም።

ይህን ፕሮቲን ለመዝጋት የሚያስፈልገው መድኃኒት በአካባቢው ሲረጭ እንደ ንብ ያሉ ሌሎች ጠቃሚ በራሪ ነፍሳትን ሳይነካ የወባ ትንኝን የመረባት ኡደት ብቻ እንደሚቀንስ የጥናት ቡድኑ ገልጿል።

አሁን ያለውን የወባ ትንኝ የማጥፊያ መድኃኒት ትንኞቹ እየተቋቋሙት እንደሆነ በዩንቨርስቲው የኬሚስትሪና የባዮ ኬሚስትሪ ኃላፊ ሮጅር ሚስ ፊልድ ተናግረዋል።

ምንም እንኳን የወባ ትንኝ ለመቶ ሺዎች ሞት ምክንያት ብትሆንም የብዝሃ ህይወት አካል በመሆኗ ትንኙን ከምድረ ገጽ የማጥፋት ዕቅድ እንደሌላቸውም ተገልጿል። (ምንጭ፡-ቶምሰን ሮይተርስ ፋውንዴሽን)