“ኤክስትራ ፍሬሽ” እና “ናቹራል” በሚል መጠሪያ የተዘጋጁ የጥርስ ማጠቢያ ፈሳሾችን ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም ማሳሰቢያ ተሰጠ

“ኤክስትራ ፍሬሽ” እና “ናቹራል” የጥርስ ማጠቢያ በሚል መጠሪያ የተዘጋጁ ፈሳሾች ህብረተሰቡ እንዳይጠቀም የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አሳሰበ፡፡

ባለስልጣኑ ኤክስትራ ፍሬሽ እና ናቹራል የጥርስ ማጠቢያ በሚል መጠሪያ የተዘጋጁ ፈሳሾች በአዲስ አበባ ከተማ ሀያት አደባይ፣ መገናኛ አደባባይ እና በፒያሳ በተዘጋጁ ባዛሮች ላይ በተደረገ የጤና ቁጥጥር ወቅት መገኘታቸው አስታውቋል፡፡

የምርቶቹ አምራቾች ስምና አድራሻ የማይታወቁ ጥራትና ደህነንነታቸው ያልተረጋገጠ በመሆኑ ህብረቱሰቡ እነዚህን ምርቶች እንዳይጠቀም ሲል አሳስቧል፡፡

በማከፋፈልና በሽያጭ ላይ ተሰማርተው የነበሩ ግለሰቦችና ምርቱ በየካ ፖሊስ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን በቀጣይ የምርቱን ምንጭ በማጣራት ተጨማሪ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጿል፡፡

ተመሳሳይ ምርቶች በሌሎች አካባቢ ወይም ባዛሮች እንዲሁም የመገበያያ ስፍራዎች ሊኖር ስለሚችል ህብረተሰቡ በአቅራቢያው ለሚገኝ የጤና ተቆጣጣሪ፣ ለፖሊስ አካላት ወይም በፌዴራል ደረጃ ለባለስልጣን መስሪያቤቱ እንዲያሳውቅ ጠይቋል፡፡

(የኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን)