የጤናው ዘርፍ የአመራር ስልጠና በመካሄድ ላይ ነው

በአገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠው የሁለተኛ ዙር የጤናው ዘርፍ የአመራር ስልጠና መርሃ ግብር በዚህ ከመላው የኦሮሚያ ክልል ለተውጣጡ አመራሮች በአዳማ ከተማ በመሰጠት ላይ ይገኛል፡፡

በባህርዳር በተሰጠው የ1ኛ ዙር ስልጠና ላይ መሳተፍ ያልቻሉ የአማራ ክልል የጤና አመራሮችም ተገኝተዋል፡፡
የትራንስፎርሜሽን እቅድ ዋና ዋና አጀንዳዎችን፣ የሴክተሩ ስትራቴጂያዊ የትኩረት አቅጣጫዎችን፣ እና ሌሎች አበይት ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ፅሑፍ በጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሰሃረላ አብዱላሂ አቅርበዋል፡፡

ወ/ሮ ሰሃረላ ባቀረቡት ፅሑፍ አሰራር እና የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማሻሻል፣ መረጃን መሰረት ያደረጉ ውሳኔዎችን መስጠት፣ የህብረተሰብ ተሳትፎና ባለቤትነት ማጠናከር የሚሉ ጉዳዮችን የዳሰሱ ሲሆን አያይዘውም በስልጤ ዞን ምእራብ አዘርነት ወረዳን በጎበኙበት ወቅት ያዩትን የህብረተሰብ ተሳትፎና የባለቤትነት ስሜት ለማሳያነት አንስተዋል፡፡

ስልጠናው ለአራት ቀናት የሚቆይ ይሆናል፡፡

(ምንጭ፡-  የጤና ሚኒስቴር)