ሀገር አቀፍ የጤናው ዘርፍ የተቀናጀ ድጋፋዊ ምልከታ ተጀመረ

ሀገር አቀፍ የጤናው ዘርፍ የተቀናጀ ድጋፋዊ ምልከታ (ሱፐርቭዥን) ተጀመረ፡፡

የጤና ሚኒስቴር በየዓመቱ የሚያደርገውን ሀገር አቀፍ መደበኛ ድጋፋዊ ምልከታ (ሱፐርቭዥን) በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

ምልከታው በሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ውስጥ በየደረጃው በሚገኙ የጤና ተቋማት በተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት ላይ እና በቤተሰብ ደረጃ የሚደረግ ነው ተብሏል፡፡ 

ለተቀናጀ ድጋፋዊ ምልከታ ወደ ክልሎችና ከተማ መስተዳደሮች ያቀኑት ቡድኖች ከጤና ቢሮ ስራ ኃላፊዎች ጋር የጋራ ውይይት አድርገው ምልከታቸውን በይፋ መጀመሩንም ነው ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ የሚያመላክተው፡፡